የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ከማህበረ ህይወት በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር ድጋፍ ለሚሹ ሴቶች የተለያዩ ግብዓቶችን አበረከተ።

የክፍለ ከተማው ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ከማህበረ ህይወት በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር ድጋፍ ለሚሹ ሴቶች ለስራ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ግብዓቶችን አበረከተ።

ግንቦት 29/2016 ዓ.ም (አቃቂ ቃሊቲ)
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ከማህበረ ህይወት በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር ድጋፍ ለሚሹ አምስት ሴቶች ለስራ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ግብዓቶችን አበረከተ።
ድርጅቱ በዛሬው ዕለት በክ/ከተማዉ ስር ከሚገኙ ወረዳዎች ተመልምለው ስልጠና ለወሰዱ አምስት ሴቶች የስራ ፍላጎታቸውን መሰረት ያደረገ የዳቦ ማጋገሪያ እና የችብስ መጥበሻ ማሽን እንዲሁም ለስራ ማስጀመሪያ የሚሆን ለእያንዳንዳቸው 4,500 ብር በጥሬ ገንዘብ በአጠቃላይ በገንዘብ ሲተመን 44,000 (አርባ አራት ሺ ብር ) ወጭ በማድረግ ድጋፍ አርገጓል።
በድጋፉ የርክክብ ስነ- ስርዓት ላይ የተገኙት የአቃቂ ቃሊቲ ክፍ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሂክማ መሀመድ ድጋፉን ላበረከተው ድርጅት ምስጋናቸውን በማቅረብ ጽ/ቤቱ በተያዘው በጀት ዓመት ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ተቋማት ጋር በመተባበር ልዩ ድጋፍ የሚሹ እናቶችን እገዛ ተደርጎላቸው ወደ ስራ ተሰማርተው ራሳቸዉንና ቤተሰቦቻቸዉን እንዲለዉጡ ለማስቻል በየወቅቱ ልዩ ልዩ ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ ተናግርዋል ።
ተቋሙ ቀደም ሲልም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና ከአረጋውያን ማህበር ጋር በመተባበር በክፍለ ከተማው ለሚገኙ 14 አረጋዉያን ለእያንዳንዳቸው 5 ዶሮ፣1የዶሮ ኬጅ፣50 ኪሎ መኖ ፣የዶሮ ውሃ መጠጫ እና የምግብ ማቅረቢያ ግብአት በአጠቃላይ በገንዘብ ሲተመን የ74,275 ብር ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
ሀላፊዋ አያይዘው ድጋፉ የተደረገላቸው ሴቶች በመረጡት የስራ ዘርፍ ወደ ተግባር በመግባት ውጤታማ በመሆን ለሌሎችም ጭምር ሰራ ዕድል በመፍጠር አርኣያ ሊሆኑ እንደሚገባ መልእክት አስተላልፈዋል።

About the Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may also like these